በቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሣለኝ አበበ የተመራ የልዑካን ቡድን ዛሬ ጠዋት በምዕራብ ሸዋ የኤጄሬ ወረዳ ማረሚያ ቤትን ተጎብኝቷል ።
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የሕግ ታራሚዎች አገልግሎት መምሪያ ላለፉት 14 ዓመታት የእንጨት መሰንጠቂያ መሣሪያ ፣የብሎኬት ማምረቻ ማሽን እንዲሁም ለመስኖ ሥራ የሚሆን የውሃ ፓምፕ ማሽኖችን በመግዛት እና በማሰልጠን የሕግ ታራሚዎች የሞያ ባለበት እንዲሆኑ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ይገኛል ።
ከሁለት ዓመት ወዲህ ደግሞ የሰላም ግንባታ እና የእርቅ አገልግሎት ሥልጠና በመስጠት ሰዎች በሠላም አብሮ እንዲኖሩ ታራሚዎች ከባላንጣዎቻቸው ጋር ጠባቸውን በእርቅ እንዲጨርሱ ከፍተኛ ሥራ እየተሠራ ይገኛል።
የዛሬው ጉብኝት እስከ ዛሬ እየተሰሩ ያሉትን ማህበራዊና መንፈሳዊ ሥራዎችን በማየት ለቀጣይነት ለማበረታታት የተሰበ ቢሆንም እግረመንገዳቸውን 250 ለሚሆኑ ታራሚዎች መጽሐፍ ቅዱሳትን በነጻ አከፋፍለዋል ።
በተጨማሪም የማረሚያ ጊዜያቸውን ጨርሰው በወጡ የቀድሞ የሕግ ታራሚዎች አማካኝነት የተተከለችውን የሆራ ቆታ የወንጌል ሥርጭት ጣቢያም ተጎብኝቷል ።