የማረሚያ ቤት አገልግሎት የትኩረት አቅጣጫዎች
- የወንጌል ሥርጭትና የደቀመዝሙርነት ሥራ ማካሄድ
- ለልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ዓውዳዊ የወንጌል ሥርጭትና የቤተክርስቲያን ተከላን ማካሄድ እንዲሁም ደቀመዛሙርት ማድረግ፡፡
- በማሕበረሰቦች ውስጥ የወንጌል አገልግሎትን የሚደግፍና የሚያሳይ ሁለንተናዊ አገልግሎት መስጠት
- በመልካም የሥራ ሥነምግባር የታነጸ ዜጋን ለመፍጠር የሥራ ፈጠራነትንና ክህሎትን ለሕግ ታራሚዎችና ለኅብረተሰቡ ማስተማር
- ለችግር የተጋለጡ ታራሚዎችና የታራሚዎችን ቤተሰቦች መደገፍ
- ለሕግ ታራሚዎች የማሕበራዊ-ሥነልቦና (ሳይኮሶሻል) ድጋፎችን መስጠት
- በቤተክርስቲያንና በማሕበረሰቦች ውስጥ ሰላምና ፍትሕ እንዲሰፍን ምዕመናንንና አገልጋዮችን በሰላም ግንባታ ማስታጠቅ
- በማረሚያ ቤቶችና ከሕግ ታራሚዎች ጋር ግንኙነት ባላቸው አካባቢው ማሕበረሰብ የሰላምና እርቅ ሥራዎችን በተሰላጠ መንገድ መሥራት
