Our Campaigns

  1. MKC
  2. Adopt Child
    Campaign has ended
  3. Medical Treatment
    Campaign has ended
  4. Donate Clothes
    Campaign has ended
  5. Shelters For Needy
    Campaign has ended

Become A Donor

Become A Donor
Lorem Ipsum is simply dummy text of the printing and typesetting industry.

Contact Info

684 West College St. Sun City, United States America, 064781.

(+55) 654 - 545 - 1235

info@zegen.com

Evangelism and Church Planting Ministry

በመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የወንጌል ሥርጭትና ቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ
1. መግቢያ
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ምድር ቀደምት ከሆኑት የወንጌል አማኝ አብያተ ክርስቲያናት አንዷ ናት፡፡ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በአመራርና በአገልግሎት ሰንሰለት የተሳሰረች ሲትሆን በዋናው ቢሮ: በቀጠና በክልሎች በአጥቢያ እና በሥርጭት ጣቢያ ተደራጅታ የወንጌልን ሥራ በስፋት በመሥራት ላይ ትገኛለች፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ከዋናው ቢሮ ጀምሮ ባሉ ሰንሰለቶች አገልግሎት በመስጠት ላይ ከሚገኙ ዋና የአገልግሎት መምሪያና ዘርፎች አንዱ የወንጌል ሥርጭትና ቤተክርስቲያን ተከላ መምሪያ ነው፡፡ የወንጌል ሥርጭትና ቤተክርስቲያን ተከላ በቤተ ክርስቲያናችን ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ ከሚሠራባቸው ዘርፎች አንዱ ሲሆን ዘርፉ በዋናው ቢሮ ደረጃ ተመሥርቶ ሥራ የጀመረው በ1976 ዓ.ም ነበር፡፡ መምሪያው የተመሠረተበት ዓላማ ደግሞ የወንጌል ሥርጭትና ቤተክርስቲያን ተከላ አገልግሎትን በተለያዩ መዕቀፎች አሳልጦና አቀናጅቶ ለማካሄድና ትውልድን በወንጌል ለመድረስና የእግዚአብሔርን መንግሥት በምድር ለመስፋፋት ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ ይህንን ዓላማ እውን ለማድረግ በመንግሥት የትምህርት ተቋማት ተመርቀዉ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ተመድበዉ ወደ ተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ለመንግሥትና ለግል ሥራ የሚሄዱትን የቤተክርስቲያናችን ምዕመናን በመከታተል የቤተክርስቲያን ተከላ ሥራዎች በቀደምት የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎችና አገልጋዮች የተለየ መሰጠት ተሠርቶ ውጤታማ ሆኖአል፡፡ የቤተክርስቲያናችን አባላት ለስራ በየተመደቡባቸው አከባቢዎች ተከታትሎ በመሄድ በግል ሕይወታቸው እንዲጸኑና ለሌሎች ሰዎችም ወንጌልን በመመስከር የቤት ኅብረቶችንና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድኖችን እንዲመሠርቱ በማድረግ እንዲሁም በጉብኝት በክትትልና በማበረታታት ወደ ወንጌል ሥርጭት ጣቢያነት እንዲያድጉ ማድረግም እንደ መልካም ስልት ተይዞ ተሠርቶበት ቤተክርስቲያናችን በዚህ ስልት በጣም ውጤታማ የሆነ ሥራ ሠርታለች፡፡ እነዚህ በወንጌል ሥርጭት ጣቢያነት የተያዙ አዳዲስ ኅብረቶች ቀስ በቀስ ወደ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አድገው እነርሱ ደግሞ ሌሎች አጥቢያዎችን በመውለድና በመስፋፋት በአሁኑ ጊዜ ለአገልግሎት ዓላማ የተተከሉ በርካታ የወንጌል ሥርጭት ጣቢያዎች አጥቢያዎች ክልሎች እና ቀጠናዎች ያሏት ትልቅ ቤተ እምነት ሆናለች፡፡
በ1980 ዓ.ም የወንጌል ሥርጭት የዘርፉ ስያሜ ተለውጦ ወቤምኮ ተባለ-ትርጉሙም የወንጌል ሥርጭትና ቤተክርስቲያን ምሥረታ ኮሚቴ ማለት ሲሆን የወንጌል ሥርጭትና ቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ የራሱ ተልዕኮ ዓላማዎችና የትኩረት አቅጣጫዎች ያሉት ሲሆን አገልግሎቱንም በሚገባ ለማከናወን በሥሩ የወንጌል ሥርጭት፣ የሚስዮናዊያን ስምሪትና ክትትል፣ስፖርት ለወንጌል አውዳዊ አገልግሎት ለቁጥር አንድና ሁለት የእምነት ክፍሎችና ድንበር ዘለል አገልግሎቶችንም በማገልገል ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት በትጋት እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚህ ስልታዊ ዕቅድ የወንጌል ሥርጭትና የቤተክርስቲያን ተከላ አገልግሎት ከዋናው ቢሮ ጀምሮ እስከ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ድረስ በሚገኙ የአመራርና የአገልግሎት ሰንሰለቶች በመናበብ እንዲሠራ የሚያግዙ አሰራሮችም ተዘርግተዋል፡፡ የወንጌል ሥርጭትና ቤተክርስቲያን ተከላ አገልግሎት በአሁኑ ጊዜ ስሙን ወንጌል ስርጭትና ተልዕኮ (ወስተ) እየተባለ ከሚታወቅበት የተሻለ ትርጉም በሚሰጥበት መንገድ ተቀይሮ ወንጌል ስርጭትና ቤተክርስቲያን ተከላ (ወስቤተ) የሚል ስያሜ ይዞ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ መምሪያውም ከዋናው ቢሮ ጀምሮ
በየደረጃው ከሚገኙ የአገልግሎት ክፍሎች ሁሉ ጋር ተጣምሮ ተቀናጅቶና ተባብሮ ታላቁ ተልዕኮ ግቡን እንዲመታ በትጋት እየሰራ ይገኛል፡፡
በመምሪያው በአሁኑ ጊዜ አራት የሙሉ ጊዜ የተሾሙ አገልጋዮች ያሉት ሲሆን በብዙ አቅጣጫ በበጎ ፈቃድ የሚያገለግሉ በርካታ ሰዎችና ወራዊ የቀለብ ድጋፍ የሚደረግላቸው 200 ገዳማ አገራዊ ሚስዮናዊያንና 4 ድንበር ዘለል ሚስዮናዊያን በዋናው ቢሮ ድጋፍ እየተደረገላቸው የተሰማሩ ሲሆን ቀጠናዎች ክልሎች አጥቢያዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካለት የላኩአቸውን ጨምሮ 1400 በላይ እንደተሰማሩ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
በመምሪያው በየዓመቱ 15 ሚሊዮን ብር ገደማ ለሥልጠናዎች፡ ለመስክ ጉብኝት፡ ለወንጌል ነክ ወርክሾፕ ለሚስዮናዊያን ወራዊ ቀለብ እና ለገጠርና ጠረፍ አካባቢዎች ሥርጭት ጣቢያዎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ሥራዎች በእግዚአብሔር እርዳታና ምህረት በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡
2. የወስቤተ ስልታዊ ዓላማዎች
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የወንጌል ሥርጭትና ቤተክርስቲያን ተከላ መመሪያ ተልዕኮውን እውን ለማድረግ የሚከተሉትን ዋና ዋና ዓላማዎች መሠረት በማድረግ ይሠራል፡፡
1. ለወንጌል ሥርጭትና ለቤተክርስቲያን ተከላ ዐውዳዊና ስኬታማ የሆኑ ስልቶችንና አሰራሮችን በመቀየስ ቤተ ክርስቲያን የተሳለጠ የወንጌል ሥርጭትና ቤተክርስቲያን ተከላ እንድትሠራ በአጽንኦት መደገፍ፡፡
2. ቤተክርስቲያንን ለአካባቢያዊ፣ ክልላዊ፣ አገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የወንጌል ሥርጭትና ቤተክርስቲያን ተከላ እንቅስቃሴ በእውቀትና በክህሎት እንድትንቀሳቀስ አቅምን መገንባት፡፡
3. ለቤተክርስቲያን የወንጌል ሥርጭትና ተልዕኮ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን (የገንዘብ፣ የቁሳቁስና ሌሎችም አስፈላጊ መሣሪያዎች) እንዲገኙ ማስተባበር፡፡
4. ለብሔራዊና ለዓለም አቀፋዊ ሚስዮናዊነትና ቤተክርስቲያን ተካላ ሸኪምና ጥሪ ያላቸውን የወንጌል መልዕክተኞች ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር በማቀናጀት፡ መላክና ሌሎችም እንድልኩ መደገፍ፡፡
3. በአገልግሎቱ ውስጥ ያሉ ፍላጎቶች ምን ምን ናቸው?
አገልግሎቱ መጠነ ሰፊ ሥራዎችን የሚፈልግ አገልግሎት እንደመሆኑ ብዙ የመንግስቱ ሠራተኞች ጌታ ሆይ እኔን ላከኝ የሚሉ መልዕክተኞች እንዲነሡና እንዲላኩ
ቤተ ክርስቲያንና መሪዎችዋ ለዚህ ተቀዳሚ ተልዕኮ ቅድሚያ በመስጠት ወንጌል ተኮር እንቅስቃሴ ማድረግ እንዲችሉ ብርቱ የጸሎት ድጋፍ ያስፈልጋል፡፡
ይህ አገልግሎት የእግዚአብሔርን ልብ የሚያድርስ የእርሱን ፈቃድ የምፈጽም ተልዕኮውን እንደ አስቸኳይነቱ መወጣት እንዲቻል ብርቱ ጸሎት ይደረግልን፡፡
እንደ ተልዕኮው ስፋት መንቀሳቀስ እንድንችል የገንዘብ ድጋፍ ያስፈልገናል ጸልዩልን
እግዚአብሔር ገንዘብ እንድትሰጡ ልባችሁን የሞላ ሁላችሁም በለጋስነት እንድትሰጡን እናበረታታለን፡፡